ቀላል የሙዝ ዳቦ አሰራር
- Dursitu Ayele
- Apr 14, 2021
- 1 min read

ብዙዎቻችን ቤት ውስጥ ዳቦ የመጋገር ልምድ ቢኖረንም ተመሳሳይ የሆኑ ቅመማቅመሞችን መጠቀም አናዘወትራለን:: ነገር ግን በቀላሉ በአቅራብያችን የምናገኘውን ሙዝ አና ሌሎች ፍራፍሬዎችን በመጠቀም ጣፋጭ የሆነ ዳቦ መጋገር አንችላለን:: የሙዝ ዳቦ በቤቴ ውስጥ አዘውትረን ከምንመገበው ቁርስ አንዱ ነው። በተጨማሪም ዘመድ ቤት ስሄድ ሙዝ በፌስታል ከመውሰድ ይልቅ በቀላሉ ይሄን ዳቦ ሰርቼ መውሰድ ያስደስተኛል።
ለማዘጋጀት የሚፈጀው ጊዜ: 10 ደቂቃ
ለማብሰል: 1 ሰዓት
አጠቃላይ: 1:10 ደቂቃ
የሚያስፈልጉ አቃዎች
ኦቨን ( ትልቁም ይሁን ትንሹ)
የዳቦ መጋገርያ የብርት ሰሃን
ማደባለቂያ ማንኪያ
ትልቅ ጎርጎአዳ ሰሃን
የሚያስፈልጉ ነገሮች
1 አንቁላል
3 በደምብ የበሰለ ሙዝ ተፈጭቶ
2 ብርጭቆ ፉርኖ ዱቄት
1 የሻይ ማንክያ በኪንግ ሶዳ
¼ የሻይ ማንክያ ጨው
¾ ብርጭቆ ሱካር
አዘገጃጀት
1- ኦቨኑን 350 ዲግሪ F ወይም 175 ዲግሪ C ላይ ማብራት።
2- በትልቅ ሰሃን ውስጥ ዱቄት ፣ በኪንግ ሶዳ አና ጨው ማደባለቅ። በሌላ ሰሃን ደግሞ አንቁላል መምታት አና ከተፈጨው ሙዝ አና ሱካር ጋር ማደባልቅ። የሙዙን ድብልቅ ወደ ፉርኖ ዱቄቱ መጨመር። በደምብ በማንክያ አደባልቆ ወደ ብመጋገርያ የብረት ሰሃን መጨመር።
3- ኦቨኑ ከሞቀ ቦሀላ ለአንድ ሰዓት ዳቦውን ማብሰል። አንደበሰለ ለማወቅ መሀሉ ላይ በቱዝ ፒክ ዎግቶ ንፁህ ሆኖ አንደወጣ ማየት። ለአስር ደቂቃ ያህል ዳቦው ከቀዘቀዘ ቦሀላ ለመመገብ ዝግጁ ይሆናል።

Comments